የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርና ምህንድስና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች
(የቀጠለ)
ለኢንዱስትሪዎቻችን ያልተጠና “ኩረጃን”ና የተናጠል ጉዞ ባህልን
በማስወገድ መቀናጀትና በአቅርቦት ሰንሰለት መመጋገብ አስፈላጊና
አዋጭ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለምሳሌ፡- ሸሚዝ የሚያመርት ፋብሪካ ለምርት ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የሚያቀርብለትን አቅራቢ
/አምራች/ ይፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሰፊው የሚታየው ባህል ግን ቀድሞ ከነበረው የሸሚዝ ፋብሪካ ጎረቤት ሌላ የሸሚዝ ፋብሪካ
መክፈት ቢሆንም የተሻለው አማራጭ ግን በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ክፍተት ባለበት ቦታ ተሰማርቶ ውጤታማ መሆን ነው፡፡(ለምሳሌ፡- ለፋብሪካው ጥሬ እቃ ማቅረብ ወይም ከፋብሪካው
ምርቱን ተቀብሎ እሴት ጨምሮ ለተጠቃሚ ማቅረብ፤ ካልሆነም ሌላ ከሸሚዝ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የስራ መስክ ላይ መሰማራት
ሊሆን ይችላል፡፡) ይህን መሰሉን የአቅርቦት ሰንሰለትን መመጋገብንና ጥምረትን መሠረት በማድረግ መሰማራት ሁሉንም አካላት የበለጠ
ትርፋማ ያደርጋል፡፡ ካልሆነ በአንድ ዓይነት የአቅርቦት ሰንሰለት
ምድብ ላይ መሰባሰብና ውስን የሆነን ደንበኛ መሻማት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ የአቅርቦት ሰንሰለት ሁነትም
የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡ ሁሉም አቅራቢ ከሆነ ማን ያመርታል? ሁሉም አምራች ከሆነ ማን ያቀርባል? ከምርት ቦታ አጓጉዞ ከሽያጭ ቦታ
የሚያደርስና የሚያከፋፍል/የሚሸጥ ከሌለ ለምንስ ይመረታል? የእነዚህ የሁሉም
የሰንሰለቱ ኣባላት የተቀናጀ ተሳትፎ የመጨረሻውን
ተጠቃሚ ደንበ,ኛ ለማርካት አስፈላጊ ነው፡፡ በመቀናጀት የተሟላና የተመረጠ አገልግሎት በመስጠት ደንበኛን ለማርካት ይቻላል፡፡ ጫማ የሚገዛ ተጠቃሚ ካልሲ እንደሚያስፈልገው ይታወቃል፡፡ ሁሉም ጫማ ብቻ አምራችና
አቅራቢ ቢሆን ካልሲ አቅራቢ /አምራች/ ባይኖር የመጨረሻው ተጠቃሚ ደንበኛ ሙሉ እርካታ ላያገኝ ይችላል፤ በጫማው ምርት ስራ
የተሰማሩ ብዙዎች ከሆኑ ሌሎች ደግሞ ለደንበኛው ተጨማሪ የሚያስፈልጉት ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ማተኮር ሊያዋጣቸው ይችላል፡፡
ይህ ሲባል ጫማ አምራች (አቅራቢ/ ስላለ ሌላ በዚህ መስክ ፈጽሞ አይሠማራ ማለት አይደለም፤ የተሻለ ምርት አቅርቦ ተወዳዳሪ
(ተመራጭ) መሆን የሚችል አካል ቢሰማራ ያወጣው ይሆናልና፡፡ (ካልሆነ በየሰፈሩ በተመሳሳይ መስክና ጊዜ ተከፍተው በዓመቱ
እንደተዘጉት ብዙ “ኮሌጆቻችን” አይነት እጣ ነው ትርፉ፡፡)
ሌላው የአቅርቦት ሰንሰለትን ቅድመ ጥምረትም ሆነ ድኅረ ጥምረት ዉጤታማ
ከሚያደርጉት ዋና ግብዓቶች መካከል የሰው ኃይል/ሃብት ዋናዉን ድርሻ ይይዛል፡፡ በኢንዳስትሪዎቻችን በተለይም በፋብሪካዎቻችን
ውስጥ ያለውን የሰው ኃይል ስናይ በአብዛኛው በ”መደበኛ”ና አስፈላጊ የትምህርት መስክና ስልጠና ውስጥ ያላለፈ መሆኑ የአቅርቦት
ሰንሰለቱን አስተዳደር ብቻ ሳይሆን የ “ውስጥ” ጥንካሬንና
ተፎካካሪነትንም ለማምጣት የአቅም ችግር እንዲኖርበት አድርጎታል፡፡ በትምህርት አቅርቦቱና አሰጣጡ ዙሪያ ,ያለው ዘርፈ ብዙ
ችግር እንዳለ ሆኖ ከየትምህርት መስኩ የሚመረቀውም አማራጭ ከማጣት አንጻር እንጂ በተለይ በፋብሪካ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ያለው
ፍላጎትና ተነሳሽነት አጠያያቂ ነው፡፡ ተገቢውን የሰው ኃይል በተገቢው ቦታ ማሰማራት ላይ ያለውም ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ
በማኅበረሰባችን ዘንድም በተለይ በአንዳንድ አከባቢ ሰፋ ባለ መልኩ በኢንዱስትሪ/ በፋብሪካ/ ውስጥ መስራት እንደ ተወዳጅ የስራ
ዘርፍ የሚመረጥ አይደለም፡፡ ከአለባበስ ጀምሮ የፋብሪካ የስራ ልብስን የለበሰ ሰው ሲታይ የሚሠጠው ግምት/”ክብር”/ አናሳ
ነው፡፡ በተለምዶ በአንዳንድ ቦታ ሲነገር እንደሚሰማው አለባበሱ “አዳፋ” የሆነና የፋብሪካ የስራ ልብስን አይነት ልብስ ለብሶ
ሲታይ “ዛሬስ የፋብሪካ ሰራተኛ መስለሃል/መስለሻል” የሚባለው የዚሁ የማኅበረሰባዊ አመለካከት ነጸብራቅ ነው፡፡ በፋብሪካ ውስጥ የሚሰሩ መሃንዲሶችንም “መሃንዲስ” መሆናቸውንና መሃንዲስ መባላቸውንም የማያውቅ የኅብረተሰብ ክፍል እጅግ ብዙ መሆኑም
አይዘነጋም፡፡
በመጨረሻም በአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ወሳኝ የሚባለውና ለአቅርቦት
ሰንሰለት ህልውና ምክንያት የሚሆነው የአቅርቦት ሰንሰለቱ ምርት/አገልግሎት/ ተጠቃሚ ደንበኛ ነው፡፡ የአቅርቦት ሰንሰለት ዋና
ዓላማም ተጠቃሚ ደንበኛን በማርካት በገበያ ላይ ተፎካካሪና ትርፋማ ሆኖ መቀጠል ነው፡፡ ስለዚህ ይህ በሰንሰለቱ “የመጨረሻ
እርከን” ላይ የሚገኘው አካል በሰንሰለቱ አልፎ የሚመጣለትን ምርት ካልተጠቀመ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ህልውና ጥያቄ ውስጥ
ይወድቃል፡፡ አንዳንድ ጥናቶችና የግል ምልከታዎች እንደሚያሳዩት በተጠቃሚው
ማኅበረሰባችን ዘንድ የሃገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ምርቶችን (የሃገር በቀል ኢንዳስትሪ) ምርትን ለመግዛት ያለው ፍላጎትም ሆነ ባህል ጎልቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ለዚህ
እንደምክንያት የሚጠቀሱ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም የምርት ጥራት ማነስንና የዋጋ መወደድ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ይሁንና አብዛኛው ተጠቃሚ
ለማለት በሚያስደፍርበት ሁኔታ የዋጋና የጥራትን ጉዳይ በትክክል ግምት ውስጥ ሳያስገባ ከ”ውጭ” የመጣን(የተመረተን) ምርት በብዛት
ሲመር,ጥ ይታያል፡፡
በአንድ ወቅት በአንድ ፋብሪካ ውስጥ የተመረቱ ሸሚዞች በላያቸው ላይ ያለውን ጽሑፍና በሸሚዙ ላይ የሚያያዘውን “ታግ” በማቀያየር ለገበያና ለእይታ በዐዉደ ርዕይ ላይ ቀርበው ሸሚዞቹን በጣም በተለያየ ዋጋ ለመሸጥ ተችሏል፡፡ የሚገርመው ሁሉም ሸሚዞች እኩል ጥራት
ያላቸው ሲሆኑ የተለያዩት ላያቸው ላይ ባለው ጸሑፍና ሸሚዞቹ ላይ በተያያዘው የተሰሩበትን ሃገር በሚገልጸው ታግ ብቻ ነበር ፡፤
ከፊሎቹ “በኢትዮጵያ የተመረተ” ና ሌሎቹ ደግሞ “በአሜሪካ
የተመረተ” የሚል ታግ ያላቸው ሲሆኑ ሸሚዞቹ የሽያጭ ዋጋቸው በእጥፍ ተለያይቶ ቢቀርብም በዋጋም ከ”አትዮጵያኖቹ” ሸሚዞች ከእጥፍ በላይ የሆኑት “አሜሪካኖቹ” ሸሚዞች በብዛት ተሸጠዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሃገር ምርትን የመጠቀም አዝማሚያ እየታየ መሆኑ
የሚያበረታታና የሚበረታታ ጅምር ሲሆን በተለያዩ ዐዉደ ርእይ ዝግጅቶችና “የኢትዮጵያን ይግዙ” አይነት የቅስቀሳ ስራዎች የሃገራችንን ተጠቃሚ ወደ ሃገር በቀል ምርቶች
እንዲያዘነብል የሚያግዙ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ የሌሎች በማደግ ላይ ያሉና ያደጉ ሃገራት ኢንዱስትሪዎች ልምድም የሚያሳየው ለኢንዱስትሪዎቹ ማደግ አካባቢያዊና ሃገራዊ ተጠቃሚ ደንበኛ መብዛቱ ውስጣዊ አቅም ፈጥረው ኢንዱስትሪዎቹን አለም
አቀፋዊ ተወዳዳሪ እንዲሆን አስችሏዋቸዋል፡፡ [p.s. ስለዚህ ሁላችንንም በተናጠል በሚያሳትፈው “የመጨረሻው” የአቅርቦት
ሰንሰለቱ ምድብ ቢያንስ ድርሻችንን እንድንወጣ ግድ ይለናል፡፡]
No comments:
Post a Comment